Blog

ወንድማገኝ ተሾመ ሲዳማ ቡናን የሊጉ ሻምፒዮን የማድረግ ብቃት አለው?

በሊጉ ከፍተኛ ልምድ ያለው አሰልጣኝ ገ/መድህን ሀይሌ ከሲዳማ ቡና ከተሰናበተ በኃላ መንበሩን ወንድማገኝ ተሾመ ተረክቦ ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል። ሲዳማ ቡና በወንድማገኝ ተሾመ ስር ከ7 ጨዋታዎችን 1 ሽንፈት እና 2 አቻ ያስመዘገበ ሲሆን ቡድኑን በሊጉ 3ተኛ ደረጃ ይዞ ነው ያጠናቀቀው። ነገር ግን አሰልጣኙ ከቀድሞ አሰልጣኝ ገ/መድህን ሀይሌ ምን የተለየ ነገር ወደ ቡድኑ ጨመረ ብለን ስንጠይቅ መልሱ የሚሆነው ምንም ነው።

አሰልጣኝ ወንድማገኝ ልክ እንደ አሰልጣኝ ገ/መድህን በ4-1-4-1 በተመሳሳይ የጨዋታ አተገባበር ነው ወደ ሜዳ የሚገባው። ቋሚ 11 ላይም አሰልጣኝ ወንድማገኝ እንደ ገ/መድህን ሁሉ ተመሳሳይ ተጨዋቾችን የተጠቀመ ሲሆን በግብ ጠባቂ ላይ በጊዜው መጥፎ ብቃት ላይ ያለውን ተክለማሪያም ሻንቆን በመክብብ ደገፋ ቀይሯል ። ሲዳማ ቡና በከፍተኛ ሁኔታ በተቸገረባቸው ጨዋታዎች አሰልጣኙ መፍትሄ ጠፍቶበት ተመልክተናል።ሲዳማ ቡና ከፍተኛ የተጨዋቾች ጥራት ያለው ቡድን ቢሆንም በእነሱ ደረጃ ላይ ያለ አሰልጣኝ ካልመጣ የሚመኘውን የሊጉን ዋንጫ ያገኛል ብላ ድረ መፅሄት ስፖርት አታስብም።

• • •

• • •

Design a site like this with WordPress.com
Get started