
እሽቴ አወቀ በእስራኤል ዋና ከተማ እየሩሳሌም ያደገ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ተጨዋች ነው። በታዳጊነቱ ለሀፖል ካታሞን, የሀፖል እየሩሳሌም ደጋፊዎች ክለባቻው በመጥፎ አመራር በመመራቱ በመሰረቱት ክለብ ተጫወተ። ሀፖል ካታሞን ከ ሀፖል እየሩሳሌም በላይ በኢኮኖሚው ሲዳብር ሀፖል እየሩሳሌምን በመግዛት አንድ ክለብ ሆኑ።
እሸቴ አወቀ በ2020/21 ውድድር ካታሞን ወደ 1ኛ ዲቪዝዮን እንዲያድግ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል። እሸቴ ክለቡ እንዲያድግ ካደረገው ጎሎች መካከል አንዱን ማስቆጠረ ችሏል።
በዚህ ዓመት በእራኤል ፕሪሜር ሊግ የመጀመሪያዎቹ ጨዋታዎች ላይ ሊጉ ውስጥ ባለው ፍጥነት እና አካል ብቃት የተነሳ ተቸግሮ ነበር። ነገር ግን በሚገርም ሁኔታ ተጨዋቹ እራሱ ላይ በመስራት የቡድኑ ዋና ተጨዋች መሆን ችሏል። ላለመውረድ በተደረጉ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ላይ ባሳየው አስገራሚ አቋም የቡድኑ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ ተመርጧል።ሀፖል እየሩሳሌምም ተርፏል።
የ23 ዓመቱ እሸቴ አወቀ የተከላካይ አማካይ ሲሆን በዚህ ዓመት በሊጉ ውስጥ ያስመዘገባቸውን ቁጥሮች እንመልከት:-.
26 ጨዋታዎች (10 በመቀየር)
1569 ደቂቃዎች በሜዳ ላይ
ከ489 ኳስ ቅብብሎቹ 396 የተሳኩ
ከ 264 ሸርታቴዎች 108 የተሳኩ
ከ 75 የአየር ኳሶች 24 አሸንፏል
እሸቴ አወቀ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን መጫወት የሚችል ሲሆን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማሻሻል የሚገባውን አሻሽሎ ተጨዋቹን ወደ ብሄራዊ ቡድን ማምጣት አለበት።
Leave a comment